About አማርኛ ቁርዓን አንቀጾች Islamic Quran
Amharic Islamic Quran Verses app provides users to knows about Quran a little bit.
ቁርዓን ከአላህ (ሱወ) ወደ ነቢዩ ሙሀመድ (ሰዐወ) ላይ የወረደ የአላህ ቃል ነው፡፡ ለዚህም ማስረጃው አላህ በቁርዓኑ ውስጥ በብዙ ቦታዎች ገልጾዋል፡፡ ቁርዓን ውስጥ ያልተገለፀ አንዳችም ነገር የለም በሱረቱል አል ነምል ላይ ማስረጃው ሰፍሮ ይገኛል፡፡ ይህ Android Application ከቁርዓን አንቀጾች ውስጥ በተወሰኑ ምድቦች አከፋፍለን ለህዝበ ሙስሊሙ ለማስተመሪያነት ለማቅረብ በተቻለን መጠን ሞክረናል፡፡ ስለ አላህ፤ ስለ መላኢካ፤ ስለ ልግስና፤ ትእዛዛት፤ ስለ ርህራሄ፤ ስለ ሞት፤ ስለ ጀነት፤ የሚያነሳሳ፤ ስለ ሰላም፤ ስለ ጸሎት፤ ስለ ቁርዓን እና ስለ እውነት በሚል ምድቦች በማከፋፈል ሱራውንና የአያ ቁጥሩን በመግለፅ ቀለል ባለመልኩ አቅርበናል፡፡ እነዚህን ምድቦች በራሳችን የመደብን አለመሆኑ ይሰመርበት፡፡ ይህን ለማድረግ ለግዜው የለንም ምናልባት ወደፊት ኢንሻ አላህ! እነዚህ ምድቦች ቁርዓኑን ይገልፃል የሚል እምነትም የለንም፡፡ ቁርዓን ጥልቅ ሚስጥር ይዞ የሚገኝ በመሆኑ እንኳን ይህች Application አይደለም ብዙ መፅሃፍትም ሊገልፁት አይችሉም፡፡
• “ይህ መጽሐፍ (ከአላህ ለመኾኑ) ጥርጥር የለበትም፤ ለፈራህያን መሪ ነው፡፡” (ሱረቱ አል-በቀራህ, 2)
• “አ.ለ.ረ (አሊፍ ላም ራ፤ ይህ ቁርኣን) አንቀጾቹ በጥንካሬ የተሰካኩ ከዚያም የተዘረዘሩ የሆነ መጽሐፍ ነው፡፡ ጥበበኛ ውስጠ ዐዋቂ ከሆነው ዘንድ (የተወረደ) ነው፡፡“ (11:1)
• “በሰማይና በምድር ውስጥ ምንም የተደበቀ ነገር የለም ገላጭ በኾነው መጽሐፍ ውስጥ ያለ ቢኾን እንጅ፡፡“ (27:75)
• “(ይህ) ወደ አንተ የተወረደ መጽሐፍ ነው፡፡ በደረትህም ውስጥ ከእርሱ ጭንቀት አይኑር፡፡(የተወረደውም) በእርሱ ልታስፈራራበትና ለምእምናን መገሠጫ እንዲኾን ነው፡፡“ (7:2)
• “ከጌታህም መጽሐፍ ወደ አንተ የተወረደውን አንብብ፡፡ ለቃላቶቹ ለዋጭ የላቸውም፡፡ ከእርሱም በቀር መጠጊያን በፍጹም አታገኝም፡፡“ (18:27)
• “እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በአላህና በመልክተኛው በዚያም በመልክተኛው ላይ ባወረደው መጽሐፍ በዚያም ከበፊቱ ባወረደው መጽሐፍ እመኑ፡፡ በአላህና በመላእክቱም፣ በመጽሐፎቹም በመልክተኞቹም፣ በመጨረሻውም ቀን፣ የካደ ሰው (ከእውነት) የራቀን መሳሳት በእርግጥ ተሳሳተ፡፡”
(4:136)
Download and install
አማርኛ ቁርዓን አንቀጾች Islamic Quran version 3.0 on your
Android device!
Downloaded 5,000+ times, content rating: Everyone
Android package:
com.deresawinfotech.quranic_verses, download አማርኛ ቁርዓን አንቀጾች Islamic Quran.apk
by S####:
የምትጠቅሱት አያዎች እና ሱራዎች አይገናኙም መልሳችሁ እዩት አፑን አስተካክሉ ጄዛኩም አላህ ኬይር